የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ሀዋሳ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
• ሎት 1፡- ሰርቨር
• ሎት 2፡- ፈርኒቸር
በዚሁ መሰረት ከላይ ለተጠቀሱ ዕቃዎች በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች:-
1. የታደሰ የዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ያልታገደ የንግድ ፍቃድ ወይም ታግዶ የነበረ ከሆነ የእገዳ ጊዜውን ስለመጨረሱ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው 4ኛ ፎቅ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል። ሆኖም 11ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሰርቨር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ለ ፈርኒቸር. 10,000 (አስር ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል።
8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በእራሳቸው ፈቃድ በጊዜው አለመገኘት የጨረታ ሳጥኑን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
9. የጨረታው አሸናፊዎች በውሉ መሰረት ግዥ የሚፈጸምባቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አቅርበው ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፈል የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. የመ/ቤቱ አድራሻ:- በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ፤ ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሺን (SBC) ቢሮ ጀርባ ባለው የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረት ልማት ቢሮ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር 046-212-71-38
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት
