በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ቃለቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ መድሐኒቶች፣ ሪኤጀንት እና የህክምና መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ስር የሚገኘው ቃለቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ መድሐኒቶች፣ ሪኤጀንት እና የህክምና መሣሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለተፈለገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
|
የሎት ቁ. |
የሎት ዝርዝር |
የሲፒኦ መጠን |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ አቅርቦት ግዥ |
20,000 |
|
ሎት 2 |
የጽሕፈት መሣሪያዎች |
5,000 |
|
ሎት 3 |
መድሐኒቶች፣ ሪኤጀንት እና የህክምና መሣሪያዎች |
100,000.00 |
|
ሎት 4 |
የፅዳት ዕቃዎች |
10,000.00 |
|
ሎት 5 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
10,000.00 |
የተዘጋጀ የተጫራቾች መመሪያ
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
4. ተጫራቹ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው መሆኑ አለበት፡፡
5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ስም በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
6. የጨረታው ጊዜ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው።
7. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ከጤና ጣቢያው ግዥ ቢሮ ቁጥር 30 ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
8. በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያምርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ከአደራጀው አካል ደብዳቤ በማጻፍ እና ለማያመርቱት ምርት (ዕቃ) እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ።
9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት እና ማስረከብ አለበት።
10. ተጫራቹ የሚያቀርቡትን የዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
11. ተጫራቹ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጨረታ ሰነዶቹ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ከማስረጃው ጋርበማደራጀት በታሸገ ፓስታ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
12. ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ክፍል ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል ወይም እረፍት የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል።
13. ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
14. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ (CPO) ዋስትና ማስዝ ግዴታ አለባቸው።
15. ተጫራቾች በአሸነፉበት 25% ወደላይ 25% ወደታች መግዛት ይችላል።
16. ተጫራቾች በሚያስገቡት ሎት 1.7 የበጀቱኝ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፡- ከቻሪሊያ ዝቅ ብሎ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ይገኛል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቃሊቲ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
