በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 የበጀት አመት በመደበኛ በጀት የወረዳውን ፍርድ ቤት ቢሮ ጥገና ለማስጠገን በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 የበጀት አመት በመደበኛ በጀት የወረዳውን ፍርድ ቤት ቢሮ ጥገና ለማስጠገን በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።
3. የታደሰ የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. የግንባታው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች አርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ለየብቻ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. በደረቅ ነክ ኮንስትራክሽን ግንባታ ከደረጃ ሰባት እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያለውና በተሰጠው የስራ ዝርዝርና ፐላን መሰረት ሰርቶ ማስረከብ የሚችል።
7. ለግንባታዉ የሚያስፈልጉት የፋብሪካ ዉጤት እና አጠቃላይ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በራሱ አቅርቦ መገንባት የሚችል።
8. የግንባታውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
9. ከአሁን በፊት በወረዳችን ግንባታ ለመስራት ውል ወስዶ በራሱ ችግር ያጓተተንና አቋርጦ የሄደን አይጋብዝም።
10. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ውል የሚወስደው በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡ እና ፍትህ ጽ/ቤት ይሆናል። አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር መሆኑን የተረዳ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከ 14/07/2018 ዓ/ም እስከ 04/08/2018ዓ/ም የማይመለስ 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል በበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 11:30 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጠቅላላው ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ በመሂ/1 ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሰ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ በመሂ/1 ማስያዝ የሚችል።
12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ05/08/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት እና የሚታሸግበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወይም ካላንደር ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ስአት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታው ማህተም ከንግድ ፍቃዱ ጋር ቀጥተኛ ተዛማጅ መሆን አለበት።
15. የጨረታ ሰነዱን በተሰጠው ዝርዝር መሰረት ስርዝ ድልዝ በሌለው መሙላት የሚችል።
16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 20 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0975643488 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የበየዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን
