Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአብርሆት ቤተመፃህፍት
  • Address 4 ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት, Phone: 0920627223
  • Website
  • Deadline31 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-31 00:00:00
  • Categories Catering And Cafeteria Services

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት በ2018 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር ለሰራተኞች የሚሆን ካፌ በካፌ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአብርሆት ቤተመፃህፍት


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018ዓ.ም

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አብርሆት ቤተመፃህፍት በ2018 በጀት ዓመት ላቀዳቸው ስራዎች በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በማወዳደር ለሰራተኞች የሚሆን ካፌ በካፌ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል። ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.     ተጫራቾች በዚህ በጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሱትን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ(በዘርፉ) የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው።

2.     ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ RE ሎት5 የካፌ አገልግሎት 20,000 ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር በተቋሙ የንግድ ባንክ አካውንት 1000738436893 ገቢ በማድረግ እና የባንክ እስቴትመንት በመያዝ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር ቢ35 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና ቢሮ ቁጥር ቢ 21 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣

4.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ፤ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።

5.     ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 59 ይከፈታል። ሆኖም እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።

6.     የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ7 ቀናት በኋላ ይመለሳል።

7.     የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ ግዥ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

8.     አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት ለአገልግሎት ለማቅረብ ምቹ ማድረግ አለበት።

9.     ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 20 62 72 23

አድራሻ 4 ኪሎ ፓርላማ ፊት ለፊት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአብርሆት ቤተመፃህፍት

Save Tender