Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ
  • Address ቴፒ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: +251912932500
  • Website
  • Deadline17 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-17 00:00:00
  • Categories Construction Works

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በምዕራብ ኦሞ ዞን ጅሙ ከተማ ላይ የመጸዳጃ ቤት፣ እና የመሸጫ ማሳያ ማዕከል አጥር ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በምዕራብ ኦሞ ዞን ጅሙ ከተማ ላይ የመጸዳጃ ቤት፣ እና የመሸጫ ማሳያ ማዕከል አጥር ግንባታ ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች በሚከተሉት መመዘኛዎች መሠረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡-

1.     ተፈላጊ መመዘኛዎች

የሥራ ዘርፉ የሕንፃ ግንባታ (BC) ወይም አጠቃላይ ግንባታ (GC) ሆኖ ደረጃው ደረጃ 7 (Grade 7) እና ከዚያ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው።

የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው፡፡

♦ የቅርብ ጊዜ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) እና በመንግሥት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችል።

2.     የግንባታው ዝርዝር ደዘት

የግንባታው ቦታ፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ጅሙ ከተማ፡፡

♦ የሥራው ዓይነት: የመጸዳጃ ቤት ግንባታ፣ እና የመሸጫ ማሳያ ማዕከል አጥር ግንባታ፡

3.     የጨረታ ሰነድ አገዛዝ እና አቀራረብ

ተጫራቾች የማይመለስ ብር [300 ብር (ሶስት መቶ ብር)] በቢሮ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000705389137 ላይ ገቢ በማድረግ የባንክ እስሊፕ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮአችን በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) መጠን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ) በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መግባት ይኖርበታል።

4.     ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ጊዜ

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ፣ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን በ 4፡30 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክፍል ይከፈታል፡፡ (22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል)።

 

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፣ ስልክ: +251912932500

 

የደቡብ ምዕራብ ክልል መንግስት ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ /አድራሻ፡ ቴፒ/

Save Tender