Tender Detail

Tender Details

  • Company Mizan Regional Veterinary Laboratory Center (የሚዛን እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል)
  • Address ሚዛን አማን ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 092 542 7273
  • Website
  • Deadline08 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-08 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሚ/እ/ጤ/ጥ/ላ/ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የዙሪያ አጥር ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Mizan Regional Veterinary Laboratory Center (የሚዛን እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሚ/እ/ጤ/ጥ/ላ/ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የዙሪያ አጥር ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

1.     ደረጃ 6GC/B.C እና ከዛ በላይ የሆነ፡፡

2.     ተጫራቾች ሰነዱን ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የብቃት ማረጋገጫ፤ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ሰርቴፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ እና የምስክር ወረቀት በማቅረብ በተቋሙ ግ/ፋ/ን ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መግዛት ትችላላችሁ፡፡

3.     የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል፡፡

4.     የጨረታ ማስመስከሪያ ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡

5.     ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ /ፋይናንሻል እና ቴክኒካል/ ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዳንዱን ለየብቻ በሰም በማሸግ በመፈረም እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም መምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል እና ኮፒ የሚል ፅሁፍ በግልፅ የሚታይ ቦታ ላይ መፃፍ አለበት፡፡

7.     ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡

8.     እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፤ የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩን ስልክ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት፡፡

9.     ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡

10. ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በተቋሙ ግ/ፋ/ን/አ/ቢሮ ቁጥር 5 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡

11. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በተቋሙ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ቢሮ ቢሮ ቁጥር 5 በጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

 

•        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የሚዛን እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብራቶሪ ማዕከል

Save Tender