የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት 1-የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማ፣ ሎት 2፡- ግማሽ ሊትር የታሸገ ንፁህ ውሃ፣ ሎት 3፡ -የተለያዩ ህትመቶች እና ሎት 4- የICT እቃ ራውተር (Router)፣ ሎት 5፡- የተለያዩ የመኪና ቅባቶች እና ደህንነት መጠበቂያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau (አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ 002/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች ሎት 1-የደንብ ልብስ እና ቆዳ ጫማ፣ ሎት 2፡- ግማሽ ሊትር የታሸገ ንፁህ ውሃ፣ ሎት 3፡- የተለያዩ ህትመቶች እና ሎት 4- የICT እቃ ራውተር (Router)፣ ሎት 5፡- የተለያዩ የመኪና ቅባቶች እና ደህንነት መጠበቂያ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
2. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል) 18ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬከቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን ያለውን አካል ፊርማና ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፒያሳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል) 18ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም C.P.O ማስያዝ አለባቸው። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
6. በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑበትን እቃዎች በወቅቱ በተገቢው የማስረከብ ግዴታ አለባቸው።
8. ከሎት 4 ውጭ ያሉትን ሎቶች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በውላቸው መሠረት በወቅቱ በሚሰጡ ትዕዛዞች ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ቀርበው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0111262185 ይደውሉ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
