የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን ያገለገሉ (three winding / coil) ትራንስፎርመሮችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ምሪ/
ግ/ጨ-5962/100/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን ያገለገሉ (three winding / coil) ትራንስፎርመሮችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ሎት
|
የዕቃው ዓይነት
|
የሚገኝበት ቦታ
|
መለኪያ
|
ብዛት
|
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ
|
የጨረታ መክፈቻ
|
|
1
|
የተለያየ መጠን ያላቸዉ ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (three winding coil)
|
አርባምንጭ ከተማ 03 ቀበሌበሚገኘዉ በተቋሙ ግምጃ ቤት
|
በቁጥር
|
37
|
100,000.00
|
መጋቢት 16 ቀን 2018ዓ.ም 8:00
|
መጋቢት 16 ቀን 2018ዓ.ም 8:30
|
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000255391422 የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ስዓት በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፤ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት በሪጅኑ ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።
7. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 046-181-5412 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አርባምንጭ ሪጅን
