Tender Detail

Tender Details


የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለቢሮ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ከዚህ በታች ባሉት በሎት የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ 01/2018

 

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ ለቢሮ ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ከዚህ በታች ባሉት በሎት የተጠቀሱትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

•        ሎት 1. የእስቴሽነሪ ዕቃዎች

•        ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች

•        ሎት 3. ፈርኒቸር

በዚህ መሠረት:-

1.     ግዥው የተ.እ.ታ የማይመለከተው ካልሆነ በስተቀር የተ.እ.ታ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ

2.     የታደሰ የንግድ ፈቃድ

3.     የንግድ ምዝገባ ሰርቴፍኬት

4.     የዓመቱ የታክስና ግብር ግዴታ የተወጡበት ክሊራንስ

5.     የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው

6.     የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች፤

7.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ 1-6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

8.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 30 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

9.     ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO /BID BOND የ90 ቀን ለሎት 1, /30,000/፣ ለሎት 2, /30,000/፣ ለሎት 3. /30,000/ ብር በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናልና 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 2 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ10 ተከታታይ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትና/ ባልተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ከሆነ/ የስራ ቀን ካልሆነ/ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።

12. መስሪያ ቤቱ ለናሙና የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ከጨረታው ሰነድ ጋር የሚገለጽ ከሆነ ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለተጠየቁት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባችሁ።

13. የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል።

14. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ :- ስልክ ቁጥር 046 220 2077

 

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

Save Tender