Tender Detail

Tender Details

  • Company የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርኘራይዝ
  • Address ኮምቦልቻ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 033 351 06 60
  • Website
  • Deadline13 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-02-13 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርኘራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች ማለትም በቆሎ፣ ብሪደር ኮንስትሬት 25% ፍርሸካ፣ ኑግ ፋጉሎ፣ በሃ ድንጋይ፤ ቶከሲን ባይንደር እና የዶሮ መኖ መያዣ ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርኘራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት የዶሮ መኖ ጥሬ እቃዎች ማለትም በቆሎ፣ ብሪደር ኮንስትሬት 25% ፍርሸካ፣ ኑግ ፋጉሎ፣ በሃ ድንጋይ፤ ቶከሲን ባይንደር እና የዶሮ መኖ መያዣ ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል; ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

4, የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርቲፊኬት የሚያቀርብ፡፡

5. የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምረው መሙላት የሚችሉ፡፡

6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የድርጅቱን ስም አድራሻ ማሕተም ፊርማ በማድረግ በሚነበብ መልኩ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ማቅረብ የሚችል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ሽያጭ እና ገበያ ልማት ደጋፊ የስራ ሂደት በሽያጭ ከፍል ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናሉን በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከ2/6/2018 እስh 6/6/2018 ዓ.ም ከጧቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

9. የተመጣጠነ የተዘጋጀ/ የዶሮ መኖ የብቃት እና የጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም 6/6/2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

1. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የዋጋውን 1/አንድ/ ከመቶ በጥሬ ገንዘብም ሆነ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

12. የእቃው ርከከብ በተመለከተ ኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ግቢ ድረስ ማስረከብ የሚችል፡፡

13. ጨረታውን ተወዳድሮ ከሚያሸንፍ አቅራቢ እስከ 50 በመቶ ተጨማሪ ማዘዝም ሆነ ቀንሶ መግዛት ይቻላል፡፡

14. የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5 ተከታታይ የሰራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/ አስይዞ ውል መግባት የሚችል፡፡

15. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 033 351 0660

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት

 የኮምቦልቻ ዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርኘራይዝ

Save Tender