Tender Detail

Tender Details

  • Company Educational Materials Production and Distribution Enterprise (የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት)
  • Address Head Office, Gurd Shola Beside of Holycity center , Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0116 -46-34 81
  • Websitehttps://empde.com.et/
  • Deadline19 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price600.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-19 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት (2018-2020) ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አይ ኤፍ አር ኤስ እና የህጋዊነት (Compliance Audit) የሚያደርጉ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና በኦዲት ቦርድ እውቅና ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሂሳቡን ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

Educational Materials Production and Distribution Enterprise (የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት)


ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ት.መ.ማ.ማ.ድ/NCB/14/2018

 

ድርጅታችን (2018-2020) ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ዓመታት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አይ ኤፍ አር ኤስ እና የህጋዊነት (Compliance Audit) የሚያደርጉ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና በኦዲት ቦርድ እውቅና ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሂሳቡን ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ ብቃት ያላቸውን የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

1.     በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የታክስ ክሊራንስ ደብዳቤ፤ የተ.እ.ታ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና የኦዲት ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን፡፡

2.     ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከ7፡30 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.     ጨረታው የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 8.00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡

5.     ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡

6.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ Tel /0116 -46-34-81 መረጃ ማግኘት ደቻሳሱ፡፡

 

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት

Save Tender