Tender Detail

Tender Details


የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለስራ የሚፈልጋቸውን ሎት 1. ፕላስቲክ ነክ የውሃ እቃዎች (HDPE & PPR Fittings)፤ እና ሎት 2. ብረት ነክ የውሃ እቃዎች (GS Fitting)፣ ሎት 3. ዲ-ሲ-አይ ውሃ እቃዎች (DCI Fitting) እና ሎት 4. ፓምፕ፣ ኬብል፣ ቦርድና ፓምፕ መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡

የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር GTWSSS/0008/2018 ዓ/ም

 

የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለስራ የሚፈልጋቸውን ሎት 1. ፕላስቲክ ነክ የውሃ እቃዎች (HDPE & PPR Fittings)፤ እና ሎት 2. ብረት ነክ የውሃ እቃዎች (GS Fitting)፣ ሎት 3. ዲ-ሲ-አይ ውሃ እቃዎች (DCI Fitting) እና ሎት 4. ፓምፕ፣ ኬብል፣ ቦርድና ፓምፕ መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

3.     የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TTN No) ያላቸው፤

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT Register/ የሆኑና

5.     የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (C P O) ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 27 ከቀን 28/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 12/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፣

7.     በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ንዑስ የስራ ሂደት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር14) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) እና አንድ ኮፒ (ቴከኒካልና ፋይናንሻል) የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ጨረታው የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡

•        የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በሀገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 3316/058 112 0697 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender