በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የህትመት ሥራዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እታዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪዎች እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በ2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የህትመት ሥራዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪዎች እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
2. የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር
3. ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ብቻ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ /ከባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነነብት እቃ ዋስትና ወይም የውል ማስከበሪያ በካሽ /BID BOND/ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስና ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁ.5 ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
8. ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችን በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እንዲሁም CPOውን ከኦርጅናሉ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ንብ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0111 26 75 10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ አጠገብ ቴሌ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 0111579568/67/0111-26-77-17
በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ደ/ት/ቤት
