Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለአሳ/ወ/ፍ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎትı እስቴሽነሪ ሎት 2 አነስተኛ ቋሚ እቃ፣ ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 ህትመት ሎት 5 የዕዳት እቃ ፤ ሎት6 መስተንግዶ ጨረታ፣ ሎት7 የተዘጋጁ የደንብ ልብስ፤ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ ብትን ጨርቅ፣ ሎት8 አውት ሶርስ (የፎት ኮፒ ማንሳት አገልግሎት) አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ ፍርድ ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ ፍርድ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለአሳ/ወ/ፍ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎትı እስቴሽነሪ ሎት 2 አነስተኛ ቋሚ እቃ፣ ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 ህትመት ሎት 5 የዕዳት እቃ ፤ ሎት6 መስተንግዶ ጨረታ፣ ሎት7 የተዘጋጁ የደንብ ልብስ፤ ጫማ፣ ሸሚዝ፣ ብትን ጨርቅ፣ ሎት8 አውት ሶርስ (የፎት ኮፒ ማንሳት አገልግሎት) አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ነበር ያላቸው፡፡

3. የግዥ መጠን ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫቱን ጨምሮ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ ደብዳቤ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /cpo/ ማስያዝ

አለባቸው ::

7. አሸናፊ ድርጅት ጽ/ቤቱ አሸናፊነቱን ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በውሉ መሰረት እቃውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. በተጫራቾች የተሞላ የጨረታ ሰነድ መ/ቤቱ ሰነዱን እንዲሸጥ ባስቀመጠው ከ 22/5/2018 ዓ/ም ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡

9. በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናና ቅጅ በማለት ሙሉ አድራሻ ስልከ አብሮ በመፃፍ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው የሚዘጋበት በ16ኛው ቀን ማለትም 6/6/2018 ዓ.ም የጨረታው ሳጥን ከጠዋቱ 4፡30 ይታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡

1. የጨረታ የመከፈቻ ቀን የህዝብ በአልና ቅዳሜ እሁድ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ የተገለፀውን ሰነድ አሳ/ወ/ፍ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይቻላል፡፡

13. አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊውን እቃ (ንብረት) አሣ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡

14. ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢያንስ ለ2 ወር የጊዜ ገደብ ያለው መሆኑን ይኖርበታል፡፡

16. በተመረጠው ናሙና መሰረት ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የአሸነፈውን ብትን ጨርቅ በሜትርቆራርጦ ማስረከብ አለበት፡፡

17. ውድድሩ በአይነት ስለሆነ ማንኛውም ተወዳዳሪ በአይነት የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ የዕቃዎቹን ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- አሽናፊው ድርጅት ጥራት ያለው እቃ በወቅቱ አስገብቶና ሂሳቡን በወቅቱ የሚያፀድቅ መሆን አለበት፡፡

በተከታታይ ቁጥር ያለው እና በስሙ የታተመ ደረሰኛ ገ/ኢ/ኮ/ጽ/ቤት የተመዘገበ ማቅረብ

አለበት፡፡

ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0922565687 /0967837826 መጠየቅ ደቻሳል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት ወረዳ ፍርድ ቤት

Save Tender