የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች በቀን 15/05/2018 ከሰዓት ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ለግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
2. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሰ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
3. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
5. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
7. አሳማኝ የሆነ ምከንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
8. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሽነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈለግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
9. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
10. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከቀን 15/05/2018 ከሰዓት 9:00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በቀን 18/05/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
N.B፡- አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቀ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
ጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
