Tender Detail

Tender Details


ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የፕላስቲክ ጀርካኖች እና ያገለገሉ የመኪና እና የፎርክሊፍት ጎማ፣ ባትሪ እና ዘይት እና የእንጨት ፓሊት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

REPI SOAP AND DETERGENT S.C (ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ረጲ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ የፕላስቲክ ጀርካኖች እና ያገለገሉ የመኪና እና የፎርክሊፍት ጎማ፣ ባትሪ እና ዘይት እና የእንጨት ፓሊት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫረቾች፡-

1.     የ2018 በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ ያለው መሆኑ ይኖርበታል።

2.     የጨረታ ማስከበሪያ በ CPO መልክ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፤

3.     ለዚህ ጨረታ ተብሎ የተዘጋጀውን ጨረታ ሰነድ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 13/05/2018 ጀምሮ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ብቻ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) ክፍለው የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

4.     ጨረታው እስከ ጥር 19,2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ጨረታው ጥር 19,2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ከሰዓት ዝግ ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 9፡00 አቅርቦትና ክምችት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።

6.     ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7.     ተጫራቾች ማንኛውንም ዋጋ ሲሞሉ ከቫት በፊት መሆን አለበት ከነ ቫቱ (VAT) ያስገባ ተጫራች ከጨረታ ዉድቅ የሆናል።

ለበለጠ መረጃ

ረጲ ሣሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ፣ አድራሻ አዲስ አበባ ጅማ መንገድ ካራ ቆሬ ሰኘላይ ቼን ክፍል ስልክ ቁጥር 0113693518 /0992921872

Save Tender