Tender Detail

Tender Details


የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት 2ኛ ዙር ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ


ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት 2ኛ ዙር ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውል

•        ሎት 1. ደንብ ልብስ 

•        ሎት 2. ህትመት

•        ሎት 3. መድሃኒት

•        ሎት 4. ጽዳት እቃዎች

•        ሎት 5. ልዩ ልዩ እቃዎች

•        ሎት 6. ለግብር እና ለደን እና ባሕር ግብዓቶች

•        ሎት 7. ለተሽከርካሪዎች ለሌሎች መጓጓዣዎች

•        ሎት 8 ለሕንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና

•        ሎት 9. ለፕላንት እና ማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት

•        ሎት 10. ለፕላንት፣ ለማሽነሪና ለመሳሪያ መግዣ

 

1.     ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን /2017/ ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋዮች መሆናቸውን የሚገልጽና፣ ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ቫት ሰርተፍኬት እና ቲን ሰርተፍኬት ያላቸው ማቅረብ አለባቸው።

2.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከመ/ቤቱ ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ማግኘት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች ለሚጫረቱት ሎት በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.     ለሕንጻ፣ ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ከደረጃ ሰባት በታች መሆን አለባቸው።

ለሎት 1 ብር 6,000.00፣ ሎት 2. 5,000.00፣ ሎት 3. 7,000.00፣ ሎት 4. 7,000.00፣ ሎት 5. 5,000.00፣ ሎት 6. 5,000፣ ሎት 7. 6,000፣ ሎት 8. 70,000፣ ሎት 9. 7000፣ ሎት 10. 10,000

5.     ተጫራቾች የሚጫረቱት የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦርጅናል ሰነድ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ላይ ኮፒ በማለት ለየብቻቸው በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁለቱም ዶክመንት ላይ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 411 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

•        ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ናሙና የሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገለጻል።

•        በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ነው።

•        የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

•        ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የግዥ መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

•        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻችን

ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011 470 08 44 መጠየቅ ይችላሉ።

 

የጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ

Save Tender