ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የዱቤ ህክምና አገልግሎት ግዥ ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለአዳማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፓርት ድርጅት
የዱቤ ህክምና አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዕ/ደ/ዕ/ት/ድ/004/2018
ድርጅታችን በ2018 በጀት ዓመት የዱቤ ህክምና አገልግሎት ግዥ ለዋናው መስሪያ ቤት እና ለአዳማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች በተመለከተ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርባል።
1. የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin) እና ቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ስለመስራቱ የሚያረጋግጡ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በገቢዎች ሚኒስቴር የዘመኑ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው በመንግስት ግዥ አቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት እና አዳማ ከሚገኘው የድርጅቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፡፡
5. ተጫራቾች በቀረበው የዕቃ ዝርዝርን መሠረት በማድረግ የሚወዳደሩበትን ነጠላ ዋጋ (unit Price) እና ጠቅላላ ዋጋ (Total price) በግልፅ በሚነበብ አሃዝ በማስቀመጥ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 ቀናት በአየርላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ይከፈታል፤ ነገር ግን የመከፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሠከረ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና በታሸገ ፖስታ አድርገው ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 250,000.00 በዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት (Emergency Relief Transport Enterprise) ስም በማዘጋጀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴከኒካል _ ፕሮፖዛል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፣ፋይናንሽያል ኮፒ በማለት ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
8. ቴክኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ከ70% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
9. ተጫራቾች የፋይናንሽያል ሰነድ ከ30% የሚገመገም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
10. የቴከኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 ወይም 51/70 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር ግምገማ ያልፋሉ፡፡
11. የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀ ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ይፈፅማል፤
12. ድርጅቱ ይህንን ጨረታ ለአሸናፊ በሚሰጥበት ጊዜ የመግዣ የነጠላ ዋጋ ሳይቀየር ብዛት በ20% ለመጨመር/ለመቀነስ መብት አለው፡፡
13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስልክ ቁጥር 0114390075/1569/3592/0114391027
ፋክስ 0114-39-63-36 ፖ.ሳ.ቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችሳሱ፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ህንጻ በስተጀርባ 70 ሜትር ገባ ብሎ ነው፡፡
ዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት
