Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፌሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251115500417
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline29 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 25,000.00 (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Health Related Services

ለወንጂ ምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ሰራተኞች የሆስፒታል ህክምና አገልግሎት ግዥ (አዳማ, LP/OT/05/SIG/2019) - የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LP/OT/05/SIG/2019

  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ወንጂ ለሚገኙ የምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ሰራተኞችና ቤተሰቦቻቸው የሆስፒታል ህክምና አገልግሎት ግዥ አዳማ ከተማ የሚገኙ የህክምና ተቋማትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከጨረታው አሸናፊ ተቋማት ጋር ለሁለት አመት የሚቆይ የዱቤ አገልግሎት ግዥ ውል መፈፀም ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ፣ በጨረታ መሳተፍ እንዲችል የድጋፍ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች/አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
    የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
    ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
    ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣
    ፊሊፐስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
    ስልክ ቁጥር +251 11 5 50 04 17
    አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተመሠከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል፡፡
  8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Sugar Industry Group seeks medical institutions in Adama to provide hospital medical services for Wonji research and training staff and their families under a two-year credit service contract. Bidders must submit a valid business license, tax clearance, VAT registration, TIN certificate, and supplier registration certificate.
Save Tender