በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አላቂ ጽዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
2. የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በገንዘብ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው።
5. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ቦ/ክ/ወ/11/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው፡፡ CPO በእያንዳንዱ ሎት መሰራት አለበት፡፡
7. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመስስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 11 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
|
ሎት ቁጥር |
ሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ.ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
3,500.00 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር / |
|
ሎት 2 |
የጽህፈት መሳሪያ |
4,000.00 /አራት ሺህ ብር / |
|
ሎት 3 |
አላቂ የጽዳት እቃ |
4,500.00 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር / |
|
ሎት 4 |
ልዩ ልዩ |
2,500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ / |
|
ሎት 5 |
ደንብ ልብስ ስፌት |
2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር / |
|
ሎት 6 |
የስፖርት ትጥቅ |
2,600.00 /ሁለት ሺህ ስድስት መቶ / |
|
ሎት 7 |
ጀኔሬተርና ሞንታርቦ ኪራይ |
3,500.00 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ / |
|
ሎት 8 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
7,000.00 /ሰባት ሺህ ብር / |
|
ሎት 9 |
ትራንስፖርት |
2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 10 |
ጭነት |
2,500.00 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ |
|
ሎት 11 |
የህፃናት ማቆያ ቦታ የተለያዩ መጫወቻ |
3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ |
8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ 11 ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 011 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
12. የሚቀርቡ ናሙናዎች በማዳበሪያ ሆኖ ቢመጣ ጥሩ ነው በፌስታል የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም።
13. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
14. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ባመረቱት ምርት ብቻ በነጻ የሚወዳደሩ ሲሆን ነገር ግን ባላመረቱት ምርት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው እና ሲፒ ኦ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ትራንስፖርት እና ጭነት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል፣ በዘርፉ የተሰማራ መሆን አለበት፡፡
• የሶስተኛ ወገን
• መንጃ ፈቃድ
• ሊብሬ ያስው መሆን አለበት።
አድራሻ፡- ሰሚት ኮንደሚንየም ሶስተኛ በር አደባባዩን ወረድ ብሎ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወ/11/ፋ/ ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 189 31 52
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት
