የኮ/ቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው የ2018 በጀት ዓመት ህትመት እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
የኮ/ቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኮ/ቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በጤና ጣቢያው የ2018 በጀት ዓመት ህትመት እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
መስፈርቶቹ
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ (የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ፍቃድ ያሳደሱ እንዲሁም የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።
2. የግዢ መጠን ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
3. በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁ 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ቀን ባይገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከፍቶ ከማወዳደር የማያግደው መሆኑ ይታወቃል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬው የጠቅላላ ዋጋውን 2% ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በኮ/ቻ 03 ጤና አጠ/ጣቢያ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይቻላል።
6. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በማስታወቂያ ቦርድ ላይ ይቆያል።
7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ የታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በኮ/ቻ 03 ጤና አጠ/ጣቢያ በግዥ/ፋ//አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 ይከፈታል።
9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት ጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም አይኖርም ያልተሞላ አይተም ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
10. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው።
12. ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የተጠየቁትን መረጃ አሟልተው ካልተገኙ በጨረታው ላይ አይሳተፉም።
13. አሸናፊው በራሱ ወጭ እቃዎችን ጤና ጣቢያው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
14. ጨረታው ለ60 ቀናት ተወስኖ ይቆያል።
15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 351 0739 / 0967 679 393 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኮ/ቻ ከተማ 03 ጤና አጠባበቅ ጣቢያ
