በኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይከሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 06/2018 የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ዉጭ የሆኑ በቢሮ፤ ዞን፤ ከተማና ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ሞተር ሳይከሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 18 /2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
1. የኤጀንሲዉ አድራሻ፣ አዲስ አበባ፣ ልደታ ከፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/ የኢትዮጲያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት/ ጨፌ እናኒ ህንጻ ከሚገኘዉ የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደርዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር - 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 –10፡30 ሰዓት ብቻ ነው።
3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ጥር 18 /2018 ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10:30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 19 /2018 ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ጥር 19 /2018 ከጠዋቱ በ5:00 ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ ከመቶ /የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O የኦሮሚያ ብሔራዊ ከልላዊ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
CPO ለማሰራት
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-15-57-70-27
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
