የእምዬ ምኒሊክ ክ/ከ አስ/ጽ/ቤት/ ለ2018ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአብክመ የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታን ከተማ የእምዬ ምንሊክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የእምዬ ምኒሊክ ክ/ከ አስ/ጽ/ቤት/ ለ2018ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
ሎት
|
የጨረታው አይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ 1%/ፐርሰንት/ብር
|
ምርመራ
|
|
1
|
ሎት 1
|
የጽሕፈት መሣሪያ/ስቴሽነሪ/
|
10000
|
|
|
2
|
ሎት 2
|
የፅዳት እቃዎች
|
1800
|
|
|
3
|
ሎት 3
|
ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
|
10000
|
|
ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላችሁ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ:
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin number/ ያላቸው፤
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- የእቃው አይነትና ዝርዝር መግስጫ/ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ብር 1% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በእምዬ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት/ ቢሮ ቁ 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ አስራ ስድስተኛው /16ኛው/ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህም 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው /ታዛቢዎች እና የውስጥ ኦዲተሮች በተገኙበት በእምዬ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት/ ቢሮ ቁ 18 በ16ኛው ቀን በ4፡30 በግልጽ ይከፈታል: ሆኖም ተጫራቾች በአከፋፈቱ ስነ-ስርአት ላይ ባለመገኘታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ግዥውን የሚፈጽመው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው መሠረት /በጥቅል/ በሎት/ ነው፡፡
- መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116 376 241 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡
- ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ሲሞሉ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በተገቢው ሞልተው ድምሩን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
በአብክመ የደ/ብርሃን ሪጂዮ ፖሊታን ከተማ የእምዬ ምንሊክ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
