አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ. የባንኩ መለያ (Bank's Logo) ታትሞባቸው የሚዘጋጁ የተለያዩ የማስታወቂያ እና የስጦታ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Bank of Abyssinia S.C. (አቢሲንያ ባንክ አ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ግአ/ግል-15/2026
አቢሲኒያ ባንክ አ.ማ. የባንኩ መለያ (Bank's Logo) ታትሞባቸው የሚዘጋጁ የተለያዩ የማስታወቂያ እና የስጦታ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | ዝርዝር | የጨረታ ማስከበሪያ | ጨረታው የሚዘጋበት ቀን | ጨረታው የሚከፈትበት ቀን |
| 1 | የተለያዩ የማስታወቂያ እና የስጦታ ዕቃዎች (Different Promotional & Giveaway Materials) | 100,000 ብር | ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት | ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎቱና ብቃቱ ያላችሁ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን:-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት (Tin certificate) ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በአቢሲንያ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 252746757 በመክፈል ከ ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት (ጠዋት 2:00-6:00 ሰዓት ፣ከሰአት ከ 7:00-11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2:00-6:00 ሰዓት) ለገሀር ከሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ ዋናው መ/ቤት ራስ ህንጻ 2ኛ ፎቅ /ብሎክB/ ግዥ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር B2-05 ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እስከ ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለጸው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የማያሟሉ ተጫራቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
- ባንኩ አንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር: +251-115584271, +251-115584462,
ኢ. ሜይል BOAprocurementoffice@bankofabyssinia.com
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ
ግዥ አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Bank of Abyssinia seeks bidders to supply various promotional and giveaway materials printed with the bank's logo. Eligible bidders must provide a renewed business license, TIN certificate, VAT registration certificate, and current tax clearance. Non-compliant bidders will be disqualified.
