Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: ----------
  • Website
  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለጽሕፈት መሣሪያ ግዥ 1.0 ፐርሰንት፣ ለህትመት እና ህትመት ውጤቶች ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለክሎሪን እና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጀንት ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/፣ ለሕንፃ መሣሪያ ግዥ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር እና ለፈርኒቸር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Chemicals And Reagents , Building Materials , Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Stationery Materials , Electronics Materials

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ህትመትና የህትመት ውጤቶች፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጄንት፣ የሕንፃ መሣሪያ፣ ፈርኒቸር እና የጽ/መሣሪያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ሀገራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በድጋሚ የወጣ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ህትመትና የህትመት ውጤቶች፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጄንት፣ የሕንፃ መሣሪያ፣ ፈርኒቸር እና የጽ/መሣሪያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስስሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል፡፡ በዚህም መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰና ሕጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ሥራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የግዥ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ሥራ ፍቃድ ኮድ መሠረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ድረስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ እና በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምር ህትመትና የህትመት ውጤቶች፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጄንት፣ የሕንፃ መሣሪያ እና የጽ/መሣሪያ ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምር ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ስርዝ ድልዝ ካለው ደግሞ ፓራፍ ማድረግ አለበት በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸላቸው ከአምስት የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ለጽሕፈት መሣሪያ ግዥ 1.0 ፐርሰንት፣ ለህትመት እና ህትመት ውጤቶች ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ሌሎች አላቂ እቃዎች፣ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ለክሎሪን እና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጀንት ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/፣ ለሕንፃ መሣሪያ ግዥ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር እና ለፈርኒቸር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግ አለበት።
  14. ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን እንዲያውቁትና የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅብዎት መሆኑን አይዘንጉ።
  15. ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ።

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender