Tender Detail

Tender Details

  • Company ጀሞ 3 ክብሎክ 138 -154 አንድነት የጋራ መኖርያ ቤቶች /ኮንዶምንየም/ ባለቤቶች ኃ/የተ/ማህበር
  • Address ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ወይም ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0922402464
  • Website
  • Deadline04 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityያቀረበውን ዋጋ 2%
  • opening date2026-01-04 00:00:00
  • Categories Finishing Work

ጀሞ 3 ክብሎክ 138 -154 አንድነት የጋራ መኖርያ ቤቶች /ኮንዶምንየም/ ባለቤቶች ኃ/የተ/ማህበር በአዋጅ ቁጥር 370/95 አንቀፅ 13 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ህንፃዎችን ቀለም ማስቀባት ይፈልጋል።

ጀሞ 3 ክብሎክ 138 -154 አንድነት የጋራ መኖርያ ቤቶች /ኮንዶምንየም/ ባለቤቶች ኃ/የተ/ማህበር


 

የጨረታ ቁጥር 06

የህንፃ ቀለም ለማስቀባት የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ጀሞ 3 ክብሎክ 138 -154 አንድነት የጋራ መኖርያ ቤቶች /ኮንዶምንየም/ ባለቤቶች ኃ/የተ/ማህበር በአዋጅ ቁጥር 370/95 አንቀፅ 13 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ህንፃዎችን ቀለም ማስቀባት ይፈልጋል። ስለሆነም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ባወጣው የህንፃ ቀለም ቅብ ደረጃ (Standard) መሰረት በማህበሩ ስር የሚገኙትን 13 (አስራ ሶስት) ባለ G+4 ህንፃዎች እና 1 (አንድ) ባለ G+1 የጋራ መጠቀሚያ ህንፃ የግድግዳ ውስጥ እና ውጭ ቀለም፤ የጎረንዳዮ ቆርቆሮና አሸንዳ እንዲሁም የመወጣጫ ደረጃ እና የመስኮት ፍርግርግ ብረቶችን ቀለም ለማስቀባት ቀለም፣ ለህንፃው መወጣጫና ሌሎች አስፈላጊ መሣሪያዎችን ሁሉንም በራሳቸው አሟልተው የሚሰሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርቲፊኬት፣
  2. የቫት እና የግብር ከፋይነት ሰርቲፊኬት (TIN Number)!
  3. ለሚከፈለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
  4. ቢያንስ በተመጣጣኝ ደረጃ ህንፃዎች /የኮንደምንየም/ ቀለም ቅብ የሰራና የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፤
  5. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ያቀረበውን ዋጋ 2% ባንክ ሲፒኦ /CPO/ አሰርቶ በማህበሩ ስም ማስያዝ የሚችል፤
  6. ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች የሚያሟሉ የስራ ተቋራጮች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት እና እሁድ ቀን ጨምሮ የጨረታ ሰነድ ከማህበሩ ቢሮ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን የሞሉትን የመጫረቻ ዋጋቸውንና አስፈላጊ ሰነዶችን በሰም በታሽገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው እሁድ ታህሳስ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧት 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀ በ3 ተከታይ የስራ ቀናት ውስጥ በማህበሩ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል። ይህ ካልሆነ ግን ስራውን በራሱ ፈቃድ እንደተወው ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበርያ ገንዘብ (CPO) ለማህበሩ ገቢ ይደረጋል።

ማሳሰቢያ፡-

  • በሌሎች ተጫራቾች ሰነድ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  • የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ያስያዙትን ሲፒኦ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
  • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር 0922402464/0911593568/0911139185 በቴሌግራም መልእክት በማስቀመጥ ወይም በጽ/ቤታችን በአካል በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።

 

አድራሻችን፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ወይም ቅድስት ማርያም ቤ/ክርስቲያን አጠገብ ይገኛል።

 

Save Tender