የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር እቃዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ 04/2018
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የፈርኒቸር እቃዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የገበሩ
- ቫት /VAT/ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያለው
- የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው
- የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ስም በተከፈተው አካውንት ቁጥር 100034760202 ላይ ገቢ በማድረግ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 230 እስሊፕ ይዛችሁ በመምጣት ሠነዱን መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ CPO /Bid Bond/ የ90ቀን ለያንዳንዱ ሎት 10,000 ብር በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናሻል ዶከመንት ኦርጂናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ ስም በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል / የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ለናሙና የሚፈልጋቸው ዕቃ ከጨረታው ሰነድ ጋር የሚገለጽ ሲሆን ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለተጠየቀው ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ እሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ጊዜያዊ ስልክ ቁጥር 046 2125584/0939126096 ይደውሉ፡፡
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
