Tender Detail

Tender Details

  • Company ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል
  • Address ሽሮሜዳ ቁስቋም 17 ቁጥር ባስ ማዞሪያ ከፍ ብሎ ውሃ ክፍሉ ጎን : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 22 821 235
  • Website
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories Finishing Work , Contractors

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለሚያስገነባው ህንፃ የፊኒሺንግ ስራን የሚሰሩ የህንፃ ግንባታ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለሚያስገነባው ህንፃ የፊኒሺንግ ስራን የሚሰሩ የህንፃ ግንባታ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ የህንፃ ግንባታ እና ፊኒሺንግ ሥራ ተቋራጮች በ7 የሥራ ቀናት Technical document and Financial proposal በአካል በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የዋጋ ዝርዝር ለማውጣት በሳይቱ ላይ ተገኝታችሁ መመልከት እና የፕላን ኮፒ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የመወዳደሪያ መስፈርቶች

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  2. Tin/ የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት
  3. የግንባታ/ የፊኒሺንግ የሥራ ተቋራጭ የሆነ
  4. አስፈላጊ የሆነ የሥራ ልምድ የሚገልፅ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
  5. የእጅ ዋጋን ሰነድ ለብቻ ማቅረብ የሚችል
  6. የእጅ ዋጋን እና የእቃ ዋጋን ሰነድ በአንድ ላይ ማቅረብ የሚችል

ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ የህንፃ ግንባታ/ የፊኒሺንግ ተቋራጮች ከዚህ በታች በተቀመጠው አድራሻ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማመልከት ትችላላሁ፡፡

አድራሻ፡- ሽሮ ሜዳ ቁስቋም 17 ቁጥር አውቶቡስ ማዞሪያ ውሃ ክፍሉ ጎን

ስልክ ቁጥር፡- 0922821235/ 0912188876

 

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል

 

Save Tender