በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ (OWNP-CWA-phase two) ፕሮግራም በወረዳ ት/ጽ/ቤት እና በወረዳ ጤና ጽ/ቤት በኩል፡- በሎት1. የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (MHM) ግንባታ በያይቄ፣ በፋራጎሳ፣ በኡጋየሁ፣ በቆላ ሙላአቶ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በዋጂፎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፤ በሎት2. የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት እና የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጓድ ግንባታ በፋራጎሳ ጤና ኬላ፣ በፉራ ጤና ኬላ፣ በዛላ ባራና ጤና ኬላ ፤በዶሼ ቀበሌ ጤና ኬላ እና የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በኡጋየሁ ቀበሌ ጤና ኬላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (ብርብር)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ (OWNP-CWA-phase two) ፕሮግራም በወረዳ ት/ጽ/ቤት እና በወረዳ ጤና ጽ/ቤት በኩል፡- በሎት1. የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ (MHM) ግንባታ በያይቄ፣ በፋራጎሳ፣ በኡጋየሁ፣ በቆላ ሙላአቶ የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በዋጂፎ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፤ በሎት2. የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት እና የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ጉድጓድ ግንባታ በፋራጎሳ ጤና ኬላ፣ በፉራ ጤና ኬላ፣ በዛላ ባራና ጤና ኬላ፣ በዶሼ ቀበሌ ጤና ኬላ እና የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ግንባታ በኡጋየሁ ቀበሌ ጤና ኬላ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- ደረጃቸው GC/BCWWC-7 እና ከዛ በላይ ሆኖ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር ወይም በመንግስት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት (E-GP system) የተመዘገበ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሠላሳ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላያ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የደረጃ ምስክር ወረቀት ያለማቅረብ ከውድድር ወጪ ያደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ቀደም የግንባታ ሥራ ውል ገብተው ያጠናቀቁበት መልካም የሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ከላዩ ላይ ተጽፎበት ሕጋዊ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ በታሽገ እንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በወረዳው ገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል እና ደረሰኙን በመያዝ የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ ከም/ዓ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማሸግ ሙሉ አድራሻውን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እንዲጨምሩ እያሳሰብን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ22ኛው የሥራ ቀን በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሣጥን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ይገኛል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0464520015/0464520009/
0970853470
በጋሞ ዞን የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት (ብርብር)
