Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/
  • Address ዱራሜ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline18 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/
  • opening date2025-12-19 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የደረቅ ጭነት ማመላለሻ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/


 

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

የጨረታ ተሳታፊዎች ዝርዝር ግዴታዎች

 

ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በትክክል አንብቦና ተረድቶ የጨረታውን ሰነድ መሙላት ይኖርበታል፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና ህጋዊ ሰውነት ምስክር ወረቀት ያለው።
  2. ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ ተቋም የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል የተሽከርካሪና የጭነት ኢንሹራንስ መድን ዋስትና የዘመኑን ማቅረብ የሚችል ወይም ላሸነፉበት ወረዳ ከጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት ካሽ አስይዞ መስራት የሚችል፡፡
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ ቢችል ይመረጣል፡፡
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፣
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2,000 /ሁለት ሺህ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም/ የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ስነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ጸዳል ኃላ/የተወሰነ ሁለገብ ህ/ስራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዱራሜ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
  8. የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ9 /ዘጠኝ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይቻላል፡፡
  9. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ጊዜ ይከፈታል፡፡
  10. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/

 

Save Tender