Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
  • Address የምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 057-660-0088
  • Website
  • Deadline24 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየጨረታው መነሻ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%)
  • opening date2025-12-24 00:00:00
  • Categories Generators , Construction Machinery , Construction Vehicle

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ የተረከባቸውን ንብረቶች በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት


 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ የተረከባቸውን ንብረቶች በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ወይም ማከራየት ይፈልጋል።

 

የተካራዩ ስም

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

የንብረት ዝርዝር

ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የጨረታ ደረጃ

የጨረታው ቀንና ሠዓት

አቶ አዱኛ ቱሊ አብዲሳ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ

Stationary Crusher Plant, Diesel Generator & Wheel Loader

ኦሮሚያ ክልል፤ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጎቶጊዳ ወረዳ፣ አብደታ ቀበሌ እና ነቀምቴ ከተማ

20,779,715.01  (ሃያ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ከ1/100)

2ኛ

ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም

ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል

 

የዝግ ጨረታ መመሪያ ፤

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋሟት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ) ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፣
  2. ንብረቱን መግዛት መከራየት የሚፈልግ የጨረታው መነሻ ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ ፒ.አ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል፣
  4. የዝግ ጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋሟት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ) ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ ሰነድ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዛበትን ዋጋ፣ ንብረቶቹን ሊገዛበት የሚፈልግበት ሁኔታ (በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ወይም ለመከራየት)፣ ቅድመ-ክፍያ መጠን እና ቀሪውን ገንዘብ የሚከፍልበት ጊዜ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ለተሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. ለዝግ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ላሸናፊው ተጫራች ከጠቅላላው ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው በራሳቸው ፈቃድ ጨረታውን የተው ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
  7. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ የጨረታው ተሳታፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ገንዘቡን ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
  8. ንብረቱን በከፈል መከራየት የሚፈልግ የጨረታው አሸናፊ የባንኩን የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት ቢያንስ ሃያ በመቶ (20%) ቅድሚያ ያሸነፈበት ዋጋ መክፈል ይኖርበታል፣
  9. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የባንኩ የማሽነሪ ኪራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ክፍያ አጠቃሎ በመክፊል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ግዴታውን ካልተወጣ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣
  10. ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ወይም ለመከራየት ከሚፈልጉ ከፍተኛውን ዋጋ ያቀረበው አካል አሸናፊ ይሆናል፣ ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ለሚፈልገው አካል ቅድሚያ ይሰጠዋል፣
  11. የጨረታ አሸናፊ ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነፃ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል፣
  12. አስራ አምስት በመቶ /15%/ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
  13. ንብረቱን ለመከራየት ከሚፈልጉ ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ ከፍተኛውን ቅድመ-ክፍያ ያቀረበው አሸናፊ ይሆናል፣
  14. ስለእያንዳንዱ ንብረት ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 057-660-0088 ወይም 057-660-0033 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡ ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉ ካሉ ዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
  15. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት

 

Save Tender