የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግስት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ1. ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 03/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግስት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት /1/ የሰራተኛ ደንብ ልብስ
- ሎት /2/ የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት /3/ ቢሮ የጽህፈት አላቂ እቃዎች
- ሎት /4/ መጽሀፍት እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች
- ሎት /5/ የህትመት ስራዎች
- ሎት /6/ አላቂ የህክምና እቃዎች
- ሎት /7/ አላቂ የጽዳት እቃዎች
- ሎት /8/ ቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት /9/ ቋሚ ዕቃ ፈርኒቸር
- ሎት /10/ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች ጥገና
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት አለባቸው።
- በሞያው ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ።
- በተጨማሪ አሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎት ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፋይናንስ እና ግዢ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል ለቋሚ እቃ በየሎት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) እና ለሌሎች እቃዎች በየሎት ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ቋሚና አላቂ እቃዎች ሳምፕል በአይነቱ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ትላልቅ ቋሚ እቃዎች ሳምፕል በፎቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውሰጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በክፍል አራት፤ ስድስት እና ዘጠኝ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በየሎት የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ ሰዓት 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ እና ግዢ ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጀት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ወዛደር የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ከተለየበት ቀን አንስቶ በ60 ቀናት ይሆናል።
- በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ሰነዱ በነጻ የሚወሰዱ ይሆናል በማያመርቱት ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾቸ በሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ባሸነፉበት የዕቃ ርክክብ የሚደረግበት ዕለት 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ቴክኒክ ኮሚቴዎች መኖራቸውን አረጋግጦ ማምጣት አለበት፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ልዩ ቦታ ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ
በስልክ ቁጥር፡- 0111-71-22-00 እና 0111-55-07-24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
