Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
  • Address ደብረዘይት መንገድ ሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 440 1913
  • Website
  • Deadline25 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10%
  • opening date2025-12-25 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles

በሸገር ከተማ ዐ/ሕግ እና በአቶ ዋጋሪ በቀለ መካከል በነበረው የወንጀል ክርክር የሸገር ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት በወንጀል መዝገብ ቁጥር 77848 የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የሰሌዳ ቁጥሩ 1-A46359 O.R ባጃጅ የወንጀል ውጤት በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ታሽጦ ገንዘቡ ለፍርድ ባለመብት ኢካፍኮ አ/ማ ገቢ እንዲደረግ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ለመሸጥ ተፈልጓል።

ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር


 

ያገለገለ ባጃጅ የሽያጭ

ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

በሸገር ከተማ ዐ/ሕግ እና በአቶ ዋጋሪ በቀለ መካከል በነበረው የወንጀል ክርክር የሸገር ከተማ ከፍተኛው ፍ/ቤት በወንጀል መዝገብ ቁጥር 77848 የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የሰሌዳ ቁጥሩ 1-A46359 O.R ባጃጅ የወንጀል ውጤት በመሆኑ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ ታሽጦ ገንዘቡ ለፍርድ ባለመብት ኢካፍኮ አ/ማ ገቢ እንዲደረግ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ለመሸጥ ተፈልጓል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፡-

  1. ደብረዘይት መንገድ ሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ ከ2፡00 – 6፡00 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 –10፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
  3. ተጫራቾች የባጃጁን ሁኔታ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጊዜ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00- 10፡30 ድረስ በሸገር ከተማ አስተዳደር ፉሪ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካቶ መቅረብ ይኖርበታል።
  6. ጨረታው ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 11 86-27-92 በመደወል መረዳት ይቻላል።

 

ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender