በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የመኪና ጎማ ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈረት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
2ተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር መደበኛ 2-2018
በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ዞን ጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመንግሥት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያስፈልጉ የመኪና ጎማ ግዥ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈረት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፤
|
ተ.ቁ |
የዕቃ/አገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO |
የማይመለስ የሰነድ መግዣ ዋጋ |
|
1 |
የመኪና ጎማ |
10,000 |
200 ብር |
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ
- ተጫራቾች የግብር ከፋይ ቁጥር /TIN/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ አሸናፊ ሲሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ ተደርጎ የውል ማስከበሪያ 20% ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ፣
- የሰነዱን ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ እንዲሁም የማይነበብ ከሆነ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋቸውን ሞልተው የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም አድርጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ቀን በኋላ በሚውለው በሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0913921119 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
