በአብክመ በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ሎት1 እስቴሽነሪ ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የመኪና እቃ፣ ሎት 5 የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ፣ ሎት- 6 የእንስሳት የህክምና መድሀኒት፣ ሎት 7 የተዘጋጀ ሶፋ፣ ሎት 8 የደንብ ልብስ የተዘጋጀ፣ ሎት፡- 9 የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 10፡- የመኪና ጎማ ሎት 11፡- የሚሰራ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ሎት 12 የውህ እቃ፣ ሎት 13 ሲሚንቶ እና ሚስማር ቆርቆሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአብክመ ሰ/ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ቡድን
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአብክመ በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ሎት1 እስቴሽነሪ ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የመኪና እቃ፣ ሎት 5 የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ፣ ሎት- 6 የእንስሳት የህክምና መድሀኒት፣ ሎት 7 የተዘጋጀ ሶፋ፣ ሎት 8 የደንብ ልብስ የተዘጋጀ፣ ሎት፡- 9 የደንብ ልብስ ጫማ፣ ሎት 10፡- የመኪና ጎማ ሎት 11፡- የሚሰራ የቢሮ ፈርኒቸር፣ ሎት 12 የውሃ እቃ፣ ሎት 13 ሲሚንቶ እና ሚስማር ቆርቆሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤
- የዘመኑ በየዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ምዝገባ፣ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ግዥው ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና መረጃ ማቅረብ የሚችል ።
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል አንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት1-7 እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ከሎት 8-13 እስከ 21ኛው ቀን 11፡30 መግዛት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ የሚወዳደሩበት ዕቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ለጽህፈት መሳሪያ 30,000፣ ለኤሌክትሮኒክስ 40,000፣ የጽዳት ዕቃ 700፣ ለመኪና ዕቃ 50,000፣ የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ 30,000፣ የእንስሳት የህክምና መድሀኒት 30,000፣ የተዘጋጀ ሶፋና ወንበር 7,000፣ የደንብ ልብስ የተዘጋጀ 3,000፣ የደንብ ልብስ ጫማ 2,000፣ የመኪና ጎማ 18,000፣ የሚሰራ የቢሮ ፈርኒቸር 2,500 የውሀ እቃ 15,000 ሲሚንቶ እና ሚስማር ቆርቆሮ 10,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ቢድ ቦንድ (በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና) ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በመቁረጥ ፖስታው ውስጥ እሽጎ/ አያይዞ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ የሞላበትን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ዘወተር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1-7 እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ከሎት 8 -13 እስከ 21ኛው ቀን 4:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች/ ህጋዊ/ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከሎት 1-7 በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ከሎት 8-13 በ 22ኛው ቀን 4:00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቹ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የተሞላው ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት በላይ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማስተካከያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ ከ 5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በደብዳቤ ማሳወቅ አለባቸው።
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን፡፡
- የአሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% በማቅረብ ዕቃዎችን አ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች ባሉ የፑል ንብረት ክፍሎች ለማስረከብ ውለታ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻ ቀን ዝግ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ በጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913161098 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተጫራቾች መመሪያ ተያይዟል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
የአብክመ ሰ/ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ን/አስ/ቡድን
