በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በኮዋሽ ፕሮጀከት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በእድገት ቀበሌ የዳሞ ተካ ወ/ስላሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስላሴ ቀበሌ የስላሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና በእስኩት ቀበሌ እስኩት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ3ቱም ት/ቤቶች የወንድ ተማሪዎችና የሴት ተማሪዎች ባለ አራት መቀመጫ ያላችው መጸዳጃ ቤቶች እና የመምህራን ባለሁለት መቀመጫ ያላቸው መጸዳጃ ቤቶች በተጨማሪም በዛራ ቀበሌ አይተማር ጤና ኬላ ባለ ሁለት መቀመጫ ያለው መጸዳጃ ቤት ለማስገንባት ተጫራቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/መ/ቁ/03/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በኮዋሽ ፕሮጀከት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በእድገት ቀበሌ የዳሞ ተካ ወ/ስላሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስላሴ ቀበሌ የስላሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና በእስኩት ቀበሌ እስኩት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ3ቱም ት/ቤቶች የወንድ ተማሪዎችና የሴት ተማሪዎች ባለ አራት መቀመጫ ያላችው መጸዳጃ ቤቶች እና የመምህራን ባለሁለት መቀመጫ ያላቸው መጸዳጃ ቤቶች በተጨማሪም በዛራ ቀበሌ አይተማር ጤና ኬላ ባለ ሁለት መቀመጫ ያለው መጸዳጃ ቤት ለማስገንባት ተጫራቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾቾ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን
1. የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው::
2 የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ
3. ተቋራጮች በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 58C/GC እና ከዛ በላይ የሆኑና የዘመኑ ግብር የመከፈል ግዴታቸዉ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸዉ::
5. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውከልና ይዘው መቅረብ አለባቸው::
6. ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ የ2018 የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
7. ተቋራጮች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት በአን ላይን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ሰርተፊኬት e-GP /Electeroic Government procurements/ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
8. የ2018 በጀት ዓመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2018 EC)
9 ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፊርማ ማኖር ግዴታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታው ቴከኒካል አና ፋይናንሻል ዶክመት ሊያቀርቡ፦
ሀ.ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንታቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት እንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርጅቱ ባለስልጣን በእያንዳንዱ ገጽ የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት እሰከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:
12. ተቋራጮች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለ ማየታቸው ከት/ቤቶቹና የጤና ኬላው ከዛራ ቀበሌ ዛራ ጽ/ቤት ጤና ኬላ የተወከለ አካል የተፈረመበት እና ማተህም የተደረገበት መረጃ በመቀበል በቴክኒካል ሰኑዱ መጨመር ግዴታ ይሆናል ይህንን የቦታ ምልከታ ያላያያዘ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
13. ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም::
14. ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ለት/ቤቶቹ እያንዳንዳቸው 21,500 (ሃያ አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) እና ለጤና ኬላው 11,500/አስራ እንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በካሽ ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴከኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸማ ቴከኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
15. ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኃላ በሚገዛቸዉ የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መበት ይኖረዋል፡፡
16 ተቋራጮች በጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረታዉ ከመከፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡
17. በጨረታዉ መወዳደር የሚፈለጉ ተጫራቾች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታዉ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 21ኛዉ ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
18. የጨረታ ሳጥኑ 21/ሃያ አንደኛ/ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰአት በጨረታዉ ኮሚቴ ታሽጎ በዛዉ እለት 8:30 ተጫራቾች /ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
1.ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉም(በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፤
2.በአፈጻጸም ምከንያት ከዚህ በፊት በወረዳው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም
3 ማንኛውም ተጫራች ለቴከኒካል ዶከመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባችኃል፡
4. ተቋራጮች የአንድ ት/ቤቱና የጤና ኬላውን ጨምሮ መስራት ይቻላል፡፡
5. የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
6. ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ ቫትን ባካተተ _ሁኔታ መሙላት ይጠበቅባችኋል ካልሆነ ቫት እንደተካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፤
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር/0961178110/0967441304/0925838193 መደወል ይችላሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት
