በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ, እንሰሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል የ2018 ዓ.ም ለእንሰሳት መኖነት የሚያገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 004/2018
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ, እንሰሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል የ2018 ዓ.ም ለእንሰሳት መኖነት የሚያገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ፡፡
ስለሆነም: -
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸዉ እንዲሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ።
2. ግብር የመክፈል ግዴታቸዉን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢዉ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታከስ ከፋይ (TIN No) የምስክር ወረቀት የአቅራቢዎች ምዝገባ/suppiler list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (80,000.00) ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ወይም የባንከ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ ::
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር በመከፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘዉ የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ከፍል በመቅረብ መዉሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸዉን የያዘዉን ሰነድ አንድ ቴከኒካል ኦሪጂናልና እንድ ቴከኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ከፍል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛዉ ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ላይ በተገለፀዉ መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
7. በጨረታ መክፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉን ከመከፈት አይስተጓጎልም።
8. ተጫራቾች የአሸነፏቸዉን አቅርቦቶች በሚሰጣቸዉ ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘዉ የእንሰሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸዉ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ።
9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114338557 / 0912065392 በመደወል መጠየቅ ይችልሉ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
