Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ
  • Address ቢሾፍቱ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114338557
  • Website
  • Deadline30 Oct 2026, 1:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 80,000.00 (በጥሬ ገንዘብ፣ CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ዕለት 8፡00 ሰዓት
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንስሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል የ2018 ዓ.ም ለእንስሳት መኖነት የሚገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ነው ፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2019

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ እንስሳት ምርምር እና እርባታ ማዕከል የ2018 ዓ.ም ለእንስሳት መኖነት የሚገለግሉ የድርቆሽ ሳር እና ጭድ ግዥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ነው ፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፤ የአቅራቢዎች ምዝገባ/sup-piler list/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር (80,000.00 ) ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴክኒካል ኦሪጅናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰአት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሕዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታ መከፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡
  8. ተጫራቾች የአሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር -0114338557 / 0913079697

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ
ቢሾፍቱ

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa University's College of Veterinary Medicine and Agriculture invites bids for hay and straw animal feed. Bidders must have a valid business license, tax compliance, supplier registration, and VAT certificate. Documents available at the Bishoftu campus.
Save Tender