በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 007/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ፡-
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 007/18 በ15/03/2018 የተለያዩ አልባሳት ፖስተር ጨርቅ ጨምሮ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ የንፅህና መጠበቂያዎችና ኮስሞትክስ፣ ስፔርፓርቶች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የመሬት ምንጣፎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ስጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ስመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
- በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥርን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
- በሀራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 አስከ ቀኑ12:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፤ ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
- ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ዕቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- ተጫራች በሀራጅ ጨረታ ለመጫረት ዕቃዎችን ለመግዛት ለሚያቀርበው ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
- በሀራጅ ጨረታ ለወጡት በእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO የዕቃውን ዋጋ 5% ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
- የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በመታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዎ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች በጨረታ ማስከበረያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
