የገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የገላን ጉራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፣01/2018
የገላን ጉራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደርየምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ የCPO ብር 24,000.00
- ሎት 2 አላቂየ ቢሮ እቃዎች የCPO ብር 20,000.00
- ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች የCPO ብር 26000.00
- ሎት 4 አላቂ የፅዳት እቃዎች የCPO ብር 20,000.00
- ሎት 5 የላብራቶሪ ኬሚካሎች እና ሞዴሎች የCPO ብር 5000.00
- ሎት 6 ልዩ ልዩ አላቂ የት/ምት መሳሪያዎች የCPO ብር 4,000.00
- ሎት 7 ቋሚ እቃዎች የCPO ብር 77,000.00
1. በመንግሥት እቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
3. የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይየሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ብር 300/ሶስት መቶ ብር በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖርበታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30-11:30 ዋጋ ቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የሥራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ዘርፍ ላይ ከላይ የተጠቀሰውን የ2%/ሁለት ፐርሰንት/CPO የብር መጠን ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን ሲቀረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ሎት ላይ ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት እቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10.ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው::
11.ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 11ኛ ቀን የሥራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 3:00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 በት/ቤቱ የግ/ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
13.ጥቃቅንና አንስተኛ ደብዳቤ ይዘው የሚቀርቡት ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ማስረጃ የሚያቀርቡ ከሆነ። እንዲሁም እራሱ በአምራችነት የተሳተፈበት ከሆነ ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረግበታል።
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ አዲሱ ካሳንቺስ ሰፈርለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0913882105/ 0114512346/ 0114510725
የገላን ጉራ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
