ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ ሎት 1፡- የህንፃ ጥገና እና ተዛማጅ እቃዎች ግዢ እና ሎት 2፡- የመኪና ግዢ (Coaster electric mid- Bus) በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
Commercial Nominees Plc (ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ)
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/14/18
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለተለያዩ ተቋማት ለሚሰጠው የሥራ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ
- ሎት 1፡- የህንፃ ጥገና እና ተዛማጅ እቃዎች ግዢ
- ሎት 2፡- የመኪና ግዢ (Coaster electric mid- Bus) (በድጋሚ የወጣ)
ድርጅታችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማሰረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማሰከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የእቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በስም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም እቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በስም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንደትወዳደሩ ይጋበዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እና ከሠዓት 7፡00-11፡00) እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሠዓት ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማሰከበሪያ ብር ለሎት 1 ብር 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር)፣ ለሎት 2 ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈ ተጫራች የእቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-555 19 11
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
