በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፀውን በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለሕክምናና ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች የሚያስፈልገውን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተገለፀውን በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ ለሕክምናና ለተለያዩ ሥራ ሂደቶች ሥራ የሚያስፈልገውን
- ፋርኒቸርና የፈርኒቸር ውጤቶች /ቋሚ የቢሮ ቁሳቁስ/ የፕላስቲክ ወንበሮች
- ለፅዳት እና ለውበት ሥራ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ (Electronic) ዕቃዎች የዲጂታላይዜሽን መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች server, Dell, desktop computer, cisco 2960-24/48/port
- የሕንፃና የቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሕትመትና የህትመት ውጤቶች
- ለተኝቶ ታካሚዎች ለምግብነት አገልግሎት የሚውል ጤፍ፣ ጥራጥሬ፣ ዳቦ፣ በርበሬ፣ ዘይት፣ ቅመማ ቅመም
- ጨርቃ ጨርቅ /ለሆስፒታሉ የደንብ ልብስ የሚውል/
- መድሃኒት
- የላቦራቶሪ ኬሚካሎችና ሬኤጀንቶች
- የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ዕቃዎች /fluorescent,lamp, change over switch 250A Electric wire /E.T.C/
- የሆስፒታሉ የጀነሬተር ጥገና ሥራ
- የሕክምና መሳሪያ፣ የአጥንት ሕክምና መሳሪያ ዕቃዎች /orthopedic materials/ እና አክሰሰሪ /መለዋወጫ የማሽኖችንና ዕቃዎችን
- በ15 (አስራ አምስት) ቀን ወደ ሀዋሳ ሳይደርስ ለማስሞላት የሚሄደውን የመኪና ኪራይ ሆስፒታሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅደም ተከተል ሁኔታዎችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን ማለትም የበጀት ዓመቱን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው።
- ጨረታውን አሸንፎ የሚያቀርበውን ዕቃ ንብረት ጥራቱን ለማረጋገጥ ናሙና ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታውን ያሸነፉ ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት ዕቃውን/ የንብረቱን እስከ ሆስፒታሉ በእራሱ ወጪ የሚያቀርብ
- አሸናፊ ሆኖ የሚጠራው ግለሰብ አቅራቢ ድርጅት የዕቃውን /የንብረቱን ጥራትና ደረጃ በጨረታ ሰነድ ላይ ሆስፒታሉ ባስቀመጠው መልኩ ውል ገብቶ በውሉ መሰረት የሚያቀርብ
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ለተከታታይ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት እና ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/ አ/ ድጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ወይም በራሳቸው የዋጋ ማቅረብያ በግልጽ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታውን እንዲያስገቡና በተገለፀው ቀን የሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አ/ደጋፊ ስራ ሂደት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዘርፍ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO በመስሪያ ቤቱ ስም ለቦና ሆስፒታል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚገባበት ቀን ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራቾች ከውድድሩ ዉጭ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታውን የሚገባበት መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀንና ሰዓት ይሆናል፡ ለተጨማሪ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0926384850/ 0968615523/0916372754 0916401599 ደውሎ መረዳት ይችላል፡፡ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ስር ቦና አጠቃላይ ሆስፒታል
