የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።
Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)
የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት)ስገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር ልዲቁኮ-01/2018
የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።
- የኮርፖሬሽኑን ሂሳብ በFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፤ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር Tax Identification Number (TIN) ያለው፤
- የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ፣
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው እካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ከአደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፣
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ወይም በሌሎች መገናኛ ብዙሃን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ድረስ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ከኮርፖሬሽኑ በመግዛት መጫረት ይቻላል።
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት "የቴክኒካል ማወዳደሪያ ሰነድ”፣ “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 29 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ በ15ኛው (አስራ አምስት) ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ወይም እለቱ የዕረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 29 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058-218-02-73 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 (058-218-05-60) በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል።
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን
