በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለፖሊስ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ ማሠራታቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የተሰራው ግንባታ የፊኒሽንግ ሥራ ያላለቀለት በመሆኑ ልዩ ልዩ የፊኒሽንግ ሥራዎች ማለትም የግድግዳ ጅብሰም ሥራ፣ የኮርኒስ ሥራ እንዲሁም የቀለም ቅብ ሥራዎችን በአገልግሎት ግዢዎችን ለመፈፀም የቁሳቁስ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በተወዳዳሪዎች በመሸፈን ለማሠራት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በማውጣት ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የሸካ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት የቤንች ሸኮ ዞን ሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለፖሊስ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ ማሠራታቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የተሰራው ግንባታ የፊኒሽንግ ሥራ ያላለቀለት በመሆኑ ልዩ ልዩ የፊኒሽንግ ሥራዎች ማለትም የግድግዳ ጅብሰም ሥራ፣ የኮርኒስ ሥራ እንዲሁም የቀለም ቅብ ሥራዎችን በአገልግሎት ግዢዎችን ለመፈፀም የቁሳቁስ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በተወዳዳሪዎች በመሸፈን ለማሠራት በግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ በማውጣት ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩትን የግንባታ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የመወዳደሪያ መስፈርቶች መሰረት እንድትወዳደሩ የሲዝ ከ/አስ/ር /ፋ/ጽ/ቤት ጥሪ ያቀርባል፡፤
የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
1ኛ. በግንባታ ሥራ ዘርፍ በጥቃ/አነ/ኢ/ፕራይዝ የተደራጁ ማኅበራት በደረጃ (09) ዘጠኝ ብቻ የተደራጁ ማህበራቶች መሆን አለባቸው፡፡
2ኛ. ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3ኛ. የንግድ ምዝገባ ስርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4ኛ. የተጨማሪ እሴት ታከስ(ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
5ኛ. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ፡፡
6ኛ. የመልካም ሥራ አፈፃጸም ማቅረብ የሚችል፡፡
7ኛ. ተጫራቾች የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
8ኛ. ከአደራጅ መ/ቤት የማህበሩን አምስት አባላቶችን ስም ዝርዝራቸውን እና የታደስ የሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲሁም ከአደራጅ መ/ቤቱ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
9ኛ. ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ከታወቀ ባንክ/ኢንሹራንስ/ወይም በጥሬ ገንዘብ የነ0,000/አስር ሺህ ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
10ኛ. ማህበሩ ከዕዳ ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፡፡
11ኛ. በማህበር ከተደራጁት ከአምስቱ አባላቶች መካከል ቢያንስ አንድ አባል ኦርጅናል ላይሰንስ ማቅረብ 12 የሲዝ ከተማ አስተዳደር የሚችሉ እና የሁሉም አባላቶች የትም/ት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ
12ኛ. ግንባታውን በሁለት ወር ጨርሶ ለማስረከብ የጊዜ ቅድመ ተከተል (ታይም ስከጁል ) ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ሥራውን ለይቶ በተቀመጠው ቢል ኦፍ ኳንቲቲ ማቅረብ የሚችል
ማሳሰቢያ-
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ቴክኒካል ማስረጃ 1(አንድ) ኦርጅናልና 2(ሁለት) ፎቶ ኮፒ እና የፋይናንሽያል ሰነድ 1(አንድ) ኦርጅናልና 2(ሁለት) ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እንዲሁም እያንዳንዱ ገጽ ላይ ፈርመው የማህበራቸውን ሕጋዊ ማህተም አድርገው በአንድ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ/ብር በመክፈል ከሲዝ ከገቢዎች ጽ/ ቤት - ቀርቦ በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
-
በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ማህበር ያሸነፈበትን የገንዘብ መጠን 20% ለማስያዝ ፍቃደኛ
-
ኮሚቴው በሚቀርቡት ሰነዶች ላይ ጥርጣሬ ካለው ኦርጅናል _ እንዲቀርብላቸው ሊጠይቁ ስለሚችሉ፡፡ ማህበራቶቹ ለሚጠየቁት ማስረጃዎች ለማቅረብ ሙሉ ፍቃደኛ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
-
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናቶች በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 8፡00 ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ኮፒ ይዘው መምጣት አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ወደ ጨረታ ሳጥን ለማስገባት ሲመጡ ተመዝግበውና ፈርመው ማስገባት አለባቸው::
-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-7770620/0911452713
የሲዝ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
