Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች ሎት አንድ የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ሎት ሁለት ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት አራት ህትመት፣ ሎት አምስት ቋሚ እቃዎች (UPS፣ ቴሌቨዥን እንዲሁም ቴሌቨዥን ማስቀመጫ ሌሎችን )፣ ሎት ስድስት የደንብ ልብስ የአደጋ መከላከያና የጤና መጠበቂያ እቃዎች፣ ሎት ሰባት የፕሪንተርየፎቶ ኮፒ እና የጄኔሬተር ሰርቪስና ጥገና ፣ ሎት ስምንት የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ (ግማሽ ሌትር ውሃ እና ቆሎ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍል ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን የሥራ መገልገያዎች ሎት አንድ የጽሕፈት መሣሪያዎች፤ ሎት ሁለት ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ ሎት ሶስት አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ሎት አራት ህትመት፣ ሎት አምስት ቋሚ እቃዎች (UPS፣ ቴሌቨዥን እንዲሁም ቴሌቨዥን ማስቀመጫ ሌሎችን )፣ ሎት ስድስት የደንብ ልብስ የአደጋ መከላከያና የጤና መጠበቂያ እቃዎች፣ ሎት ሰባት የፕሪንተርየፎቶ ኮፒ እና የጄኔሬተር ሰርቪስና ጥገና ፣ ሎት ስምንት የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ (ግማሽ ሌትር ውሃ እና ቆሎ/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1. የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መረጃውን ማቅረብ የሚችል።

2. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠማስረጃ ማቅረብ።

3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት።

4. ማንኛውም ተጫራች 200 /የሁለት መቶ ብር /በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በሂሳብ ቁጥራችን 1000383805035 በማስገባት እስሊፑን ይዘው የጨረታውን ሰነድ በሥራ ሰዓት ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት ዋናውንና ኮፒውን የሚወዳደሩበትን ዋጋበታሸገ ፖሰታ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማዘጋጀት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ ከ ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡ 30 ይከፈታል ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል። በተጨማሪም የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በጨረታ ሰነድ የሚገለፅ ይሆናል ።

8. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለተጨማሪ መረጃ፡

011-6-73-43- 16/011-6-73-21-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል። በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አድራሻ፡-ሲኤምሲ ሚካኤል ፊት ለፊት ድልድዩ አጠገብ ዴሉክስ ፈርኒቸር ጀርባ ያለው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የስሚ ኩራ ክፍስ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Save Tender