Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ
  • Address ቢሾፍቱ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114338557
  • Website
  • Deadline30 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security138,681.00 /አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር/
  • opening date2025-10-30 00:00:00
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የዶሮ መኖዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ቢሾፍቱ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨረታ ቁጥር እ/ህ/ግ/ኮ 002/2018

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የዶሮ መኖዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው አንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ከታወቀ የዶሮ መኖ የምርመራ ናሙና ሰርተፍኬት መስጠት ከሚችሉ የግልም ሆነ ከመንግስት ተቋም ማቅረብ አለባቸው።
  3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የታክስ ከፋይ (Tin No) የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ /EGP/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 138,681.00 /አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰማኒያ አንድ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) /የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕከምና እና ግብርና ኮሌጅ ግዥ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘውን ሰነድ አንድ ቴከኒካል ኦሪጂናልና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እና አንድ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሽያል ኮፒ በእናት ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 7፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኮሌጁ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ለመጫረት ያቀረቧቸውን እቃዎች ናሙና በሙሉ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናትና ሰዓት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡00 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው መዝጊያ ሰዓት ታሽጎ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  9. በጨረታ መከፈቻ ቀኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም።
  10. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን አቅርቦቶች በሚሰጣቸው ትዕዛዝ መሰረት በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የእንሰሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 0114338557/0912065391

 

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ

ቢሾፍቱ

 

Save Tender