የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታከስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመከፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከአል ቦርግ ሜዲካል ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማህበር (የህከምና መሣሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች)፤ ከኡኑፕሬሳ ኮንስትራክሽን እና ከሰንራይዝ ስቲልነስ ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር(ኮምፒውተር ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች) እንዲሁም ከሲቲ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ከፓትሮል የጥበቃ አገልግሎት፣ ከሙሂባ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከአቶ ተከኤ ዘርአይ፣ከጋንፋር ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ሜጋ ሶርስ ማኑፋከቸሪንግ የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Ministry of Revenues (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በኢትዮጵያ ፌዱራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሲክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን የህክምና መሣሪያዎች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች የተለያዩ ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ 02/2018
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታከስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመከፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ከአል ቦርግ ሜዲካል ሴንተር ኃ/የተ/የግ/ማህበር (የህከምና መሣሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች)፤ ከኡኑፕሬሳ ኮንስትራክሽን እና ከሰንራይዝ ስቲልነስ ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር(ኮምፒውተር ፕሪንተር እና የመቁረጫ ማሽኖች) እንዲሁም ከሲቲ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ፣ ከፓትሮል የጥበቃ አገልግሎት፣ ከሙሂባ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፤ ከአቶ ተከኤ ዘርአይ፣ከጋንፋር ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ሜጋ ሶርስ ማኑፋከቸሪንግ የተያዙ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦
1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት)ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታው የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶች መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
የገቢዎች ሚኒስቴር |
የህክምና መሳሪያዎች ና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ፣የመቁረጫ ማሽኖች እና የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 15 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00ሰዓት ህንፃ “ለ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከታከስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Mistry of Revenue) በባንh አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀን (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ:- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቶች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት/ ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ።
6. የግልፅ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በCPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11 ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-84-90 ኮድ (2044) (2045) (2046) የውስጥ መስመር(EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር
