የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለጥገና ጽ/ቤቱ እና ለክላስተር ፐሮጀክቶች መንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጎ/ገ/መ/03/2018 ዓ/ም
የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለጥገና ጽ/ቤቱ እና ለክላስተር ፐሮጀክቶች መንገድ ግንባታና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚቀርቡት ተሸከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
- የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትከከል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ለሰርቪስ መኪና በቀን፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለውሃ ቦቴ በሰዓት፣ ገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ እና ሎቤድ በኪ.ሜትር ብር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስድሳ) ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እውቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጥገና ጽ/ቤቱ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000143479138 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 19 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ03/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/02/2018 ዓ.ም ጎጃም ጥገና ጽ/ቤት ደ/ማርቆስ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን ሰነዳቸውን በአግባቡ በመጠረዝ በፖስታ በማሸግ የተሟላ አድራሻ በመፃፍ በሁለት ፓስታ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ተዘጋጅቶ ከግዥ ፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 18/02/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በአካል በመገኘት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጥገና ጽ/ቤቱ ግዥ ፋይ ንብረት አስተዳደር ደጋፈ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በ18/02/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የዋጋ መሙያ ቅፁ ላይ ስርዝ ድልዝ እና ፍቀት ካለው ፊርማ ያለው ቢሆንም ስርዝ ድልዝ ባለው ቦታ ላይ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይደረጋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-771-1818 በመደ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎጃም ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት
