የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ግንባታ ጥገና ፕሮጀክት ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
የመጀመሪያ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/003/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ግንባታ ጥገና ፕሮጀክት ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች ማሠራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልሉ ውስጥ መንገድ የሚገኝበት ወረዳ |
መንገድ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
ሎት1 |
መጀ ግርጃ |
አሮረሳ ሆኮ |
9 |
|
መጆ ዳኤላ |
አሮረሳ ዳኤላ |
10 |
|
|
ግርጃ ኦድ ቦኮ |
ዳራሆኮ |
7 |
|
|
ሎት2 |
ታንካሮ ዳማካላ አሳራዶ ወዩ |
ሻፋሞ |
8.5 |
|
ቦና 01 ቡርሳ |
ቦና ዙርያ ቡርሳ |
10.5 |
|
|
ሎት3 |
ጋሳ ሀላቃ ቦርፈ |
ሀገር ሰላም አለታ ወንዶ |
5 |
|
ሳፋ ተፈር ከላ ቱላ |
ዳራ ኦትልቾ |
7 |
|
|
ሎት4 |
ጭር ላሌሳ ጉ ሔማ ሎት -1 |
ጭረ |
16 |
|
ጭር ላሌሳ ጉ ሔማ ሎት -2 |
ጭረ |
16 |
|
|
አባያ ወታራ ጋንዶ |
ወንዶ ገነት |
13.5 |
|
|
ሎት5 |
ግኬ አቶዬ |
ወንዶ ገነት |
5 |
|
ይርባ 01 ኦልካ ዳንሽ |
ቦርቻ/ዳራራ |
10.5 |
|
|
ሎት6 |
ዶሬ ባፋኖ ሻማና |
ሀዋሳ ዙሪያ |
13.5 |
|
|
ማንቾ ጠረምቦ |
ማልጋ |
10 |
|
ሎት7 |
ጉጉማ ዳኛንቼ ጉፋቼ |
ማከልጋ |
8 |
በዚህ መሰረት ፡-
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሆን አለባቸው።
- ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስራት ዘመን እ.ኤ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ የተሸከርካሪ የመጫን አቅም=14m3 መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ከየተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም E-trade ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ ለብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አዲስ ስራ ፍቃድ እና ስራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻፀም ችግር ምክንያት ማስጠንቂያ ሥራውን ያላጠናቀቁና ውሉ የተቋረጠ የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነድን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በድጋሚ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፋይናንሻል አንድ ዋና ወይም ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና/ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 እስከ 6:00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት፡፡
- ጨረታ በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማከበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
