Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline17 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityከጠቅላላ ዋጋ 0.5%
  • opening date2025-10-17 00:00:00
  • Categories Vehicles Rent , Cargo Vehicle , Construction Vehicle

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢያዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


 

ለሁለተኛ ዙር የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር፡-ሲ/መ/ባ/001/2018

 

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነሎደሩ አቅራቢያዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ ተከራይቶ ማሠራት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የፕሮጀክቱ ስም

በክልሉ ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ

የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ

1

ባሌላ መገንጠያ ዳራራ ጩኮ ሎት 2

ጩኮ

10

2

ወታራሬሳ ጉጉማ

ማልጋ

8

3

ሀረር ሰላም ጋታማ

ሁላ

13.3

4

ጎርቼ ሀሮሽፋ ቱትቻ ጠጥቻ

ቡርሳ/ጠጥቻ

24.5

5

ባርቱ ቡክቶ

ሎካ አባያ

15

6

ቃባዶ አበራ ሁላ

ዳራ/ዳራ አትልቾ

30

7

አለታ ወንዶ ሀዋጃ ባርጎ ሜጫ

አ/ወንዶ/ቡርሳ

16

8

ሻንታዌነ ዳላቻ ቡራ

ቦንሳ/ቡራ

12

 

ስለዚህ

  1. ኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና መገልገያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው
  2. ገልባጭ መኪና እስከነሎደር የስሪት ዘመን እ.አ.እ 2012 እና ከዚያ በላይ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም14m³ የሆነ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ መመዝገብ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪኖች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ (ውልና ማስረጃ) የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. አዲስ ስራ ፍቃድ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ከአንድ መንገድ ብቻ እንዲሁም የሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች ደግሞ ሁለት መንገድ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  5. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ አፈጸጸም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ሥራውን ያላጠናቀቱና ውሉ የተቋረጠበት የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  8. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፋይናንሻል አንድ ዋና ወይም ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት፡፡
  9. ጨረታ በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል
  10. በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ህጎች አለማከበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተበሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446

 

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን

 

Save Tender